ዘፍጥረት 29:35 - Compare All Versions

ዘፍጥረት 29:35 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እንደ ገና ፀንሳ አሁንም ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ “እንግዲህ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስሙንም ይሁዳ ብላ ጠራችው። ከዚያም በኋላ መውለድ አቆመች።

ዘፍጥረት 29:35 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እንደገና ፀነሰችና ወንድ ልጅ ወለደች፤ “አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።

ዘፍጥረት 29:35 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ በዚ​ህም ጊዜ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ” አለች፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራ​ችው። መው​ለ​ድ​ንም አቆ​መች።

ዘፍጥረት 29:35 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ደግሞም ፀነስች ወንድ ልጅንም ወለደች በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።

ዘፍጥረት 29:35 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፥ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።