ዘፍጥረት 18:22-33

ዘፍጥረት 18:22-33 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሰዎ​ቹም ከዚያ በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወደ ሰዶም መጡ፤ አብ​ር​ሃም ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር። አብ​ር​ሃ​ምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይ​ሁን። አምሳ ጻድ​ቃን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠ​ፋ​ለ​ህን? ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንስ በእ​ር​ስዋ ስለ​ሚ​ገኙ አምሳ ጻድ​ቃን አት​ም​ር​ምን? አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “በሰ​ዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድ​ቃን ባገኝ ከተ​ማ​ውን ሁሉ ስለ እነ​ርሱ አድ​ና​ለሁ።” አብ​ር​ሃ​ምም መለሰ፤ አለም፥ “እኔ አፈ​ርና አመድ ስሆን ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እና​ገር ዘንድ አሁን ጀመ​ርሁ፤ ከእ​ነ​ዚያ አምሳ ጻድ​ቃን አም​ስት ቢጐ​ድሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሁሉ በጐ​ደ​ሉት በአ​ም​ስቱ ምክ​ን​ያት ታጠ​ፋ​ለ​ህን?” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከዚያ አርባ አም​ስት ባገኝ ስለ እነ​ርሱ አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “ከዚያ አርባ ቢገ​ኙሳ?” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ለአ​ር​ባው ስል አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም እን​ደ​ገና ነገ​ሩን ደገመ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ሠላ​ሳው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። ደግ​ሞም፥ “እነሆ፥ ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እነ​ጋ​ገር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ካገ​ኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገ​ኙሳ?” አለው። እር​ሱም፥ “ስለ ሃያው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “አቤቱ እን​ደ​ገና እና​ገር ዘንድ ፍቀ​ድ​ልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ንግ​ግ​ሩን በጨ​ረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።

ዘፍጥረት 18:22-33 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆመ ነበር። አብርሃምም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ ዐብረህ ታጠፋለህን? ዐምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ ዐምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን ይቅር አትልምን? እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?” እግዚአብሔርም፣ “በሰዶም ከተማ ዐምሳ ጻድቃን ባገኝ ለእነርሱ ስል አገሪቱን በሞላ እምራለሁ” አለ። ደግሞም አብርሃም እንዲህ አለ፤ “እኔ ከንቱ፣ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታ ጋራ ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤ ለመሆኑ ከዐምሳው ጻድቃን ዐምስት ቢጐድሉ በዐምስቱ ሰዎች ምክንያት መላ ከተማዋን ታጠፋለህን?” እርሱም፣ “አርባ ዐምስት ጻድቃን ባገኝ አላጠፋትም” አለ። አብርሃምም እንደ ገና፣ “ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ለአርባው ስል እምራታለሁ” አለ። ደግሞም አብርሃም፣ “ጌታዬ አይቈጣ፤ እባክህ ልናገር፤ ሠላሳ ጻድቃን ብቻ ቢገኙስ?” እርሱም፣ “ሠላሳ ባገኝ አላጠፋትም” ብሎ መለሰ። አብርሃምም፣ “ከጌታዬ ጋራ እናገር ዘንድ መቼም አንዴ ደፍሬአለሁና ምናልባት ሃያ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ሃያ ቢገኙ፣ ለእነርሱ ስል እምራታለሁ” አለ። አብርሃምም፣ “ጌታዬ አይቈጣ፤ አንድ ጊዜ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እርሱም “ስለ ዐሥሩ ስል አላጠፋትም” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋራ ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

ዘፍጥረት 18:22-33 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር አብርሃምም ቀረበ አለም፦ በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን? አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህብ? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርስ አይፈርድምን? እግዚአብሔርም፤ በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምስ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ አለ። አብርሃምም መለስን አለም፤ እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤ ከአምሳው ጻድቅን አምስት ቢጎድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን? ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም አለ። ደግሞም ተናገረው እንዲህም አለ፤ ምናልባት ከዚይ አርባ ቢገኙሳ? እርሱም ለአርባው ስል አላደርገውም አለ። እርሱም ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ። ደግሞም፤ እነሆ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ? አለ። እርሱም፤ ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም አለ። እርሱም፥ እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፤ ምናልባት ከዚያ አሥር አላጠፋትም አለ። እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።

ዘፍጥረት 18:22-33 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ በኋላ ሁለቱ ሰዎች ወደ ሰዶም ለመሄድ ተነሡ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆመ ቈየ፤ ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ በደል የሌለባቸውን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህን? በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን? በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?” እግዚአብሔርም “በሰዶም ከተማ ውስጥ በደል ያልሠሩ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ባገኝ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን ፈጽሞ አላጠፋም” አለ። አብርሃም እንደገና እንዲህ አለ፤ “እኔ ትቢያና ዐመድ የሆንኩ ከንቱ ሰው፥ ከጌታዬ ጋር በድፍረት በመነጋገሬ ይቅር በለኝ፤ ነገር ግን የደጋግ ሰዎች ቊጥር ኀምሳ መሆኑ ቀርቶ አርባ አምስት ቢሆን፥ አምስት ስለ ጐደለ ከተማይቱን በሙሉ ታጠፋለህን?” እግዚአብሔርም “አርባ አምስት ደጋግ ሰዎች ባገኝ ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። አብርሃምም “አርባ ብቻ እዚያ ቢገኙስ?” ብሎ እንደገና ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አርባ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ፤ እንደገና ልናገር፤ ምናልባት ሠላሳ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ሠላሳ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ አሁንም እንደገና በመናገሬ ይቅር በለኝ፤ ምናልባት ኻያ ቢገኙስ?” አለ፤ እግዚአብሔርም “ኻያ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ አንድ ጊዜ ልናገር፤ ዐሥር ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ዐሥር ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ተነጋግሮ ካበቃ በኋላ ከዚያ ስፍራ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

ዘፍጥረት 18:22-33 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ፥ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር። አብርሃምም ቀረበ ዓለም፦ “በውኑ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ታጠፋለህን? አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህን? ከተማይቱንስ በእርሷ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?” እግዚአብሔርም፦ “በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ” አለ። አብርሃምም መለሰ ዓለም፦ “እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥ ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን?” “ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም” አለ። ደግሞም ተናገረው፥ እንዲህም አለ፦ “ምናልባት ከዚያ አርባ ቢገኙሳ?” እርሱም፦ “ለአርባው ስል አላደርገውም” አለ። እርሱም፦ “ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም” አለ። ደግሞም፦ “እነሆ፥ ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥ ምናልባት ከዚያ ሀያ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሀያ ቢገኙ ስለ ሀያው አላደርገውም” አለ። እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ። እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፥ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።