ሐዋርያት ሥራ 4:8-10 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 4:8-10 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚህ ጊዜ፣ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ፤ ዛሬ ለዚህ ሽባ ሰው ስለ ተደረገው በጎ ሥራ፣ እንዴት እንደ ዳነ የምትጠይቁን ከሆነ፣ እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ግን ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መዳኑንና ፊታችሁ መቆሙን እናንተም ሆናችሁ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይህን ይወቅ።

ሐዋርያት ሥራ 4:8-10 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ! እኛ ዛሬ የምንጠየቀው ለአንድ ሽባ ሰው ስለ ተደረገለት መልካም ሥራና በምን ዐይነት ሁኔታ እንደ ዳነ ነው። ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።

ሐዋርያት ሥራ 4:8-10 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤ ዛሬ ለበ​ሽ​ተ​ኛው በተ​ደ​ረ​ገው ረድ​ኤት ምክ​ን​ያት በእ​ና​ንተ ዘንድ እኛ የሚ​ፈ​ረ​ድ​ብን ከሆነ እን​ግ​ዲያ ይህ ሰው በምን ዳነ? እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን ሁሉ፥ እና​ንተ በሰ​ቀ​ላ​ች​ሁት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊ​ታ​ች​ሁም እንደ ቆመ በር​ግጥ ዕወቁ።

ሐዋርያት ሥራ 4:8-10 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለ ተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደዳነ ብንመረመር፥ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።

ሐዋርያት ሥራ 4:8-10 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደ ዳነ ብንመረመር፥ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።