ሐዋርያት ሥራ 4:13-14 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 4:13-14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋራ እንደ ነበሩም ተገነዘቡ። የተፈወሰውን ሰው እዚያው ከእነርሱ ጋራ ቆሞ ስላዩት የሚናገሩበትን ሰበብ ዐጡ።

ሐዋርያት ሥራ 4:13-14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረት መናገራቸውን የሸንጎ አባሎች ባዩ ጊዜ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ያውቁ ስለ ነበረ ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ዐወቁ፤ የዳነውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ በማየታቸው በእነርሱ ላይ የሚሉትን አጡ።

ሐዋርያት ሥራ 4:13-14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ። ያን የዳ​ነ​ውን ሰውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ በአ​ዩት ጊዜ የሚ​ሉ​ትን አጡ።

ሐዋርያት ሥራ 4:13-14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤ የተፈወሰውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ሲያዩ የሚመልሱትን አጡ።

ሐዋርያት ሥራ 4:13-14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፤ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤ የተፈወሰውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ሲያዩ የሚመልሱትን አጡ።