2 ቆሮንቶስ 1:21-22
2 ቆሮንቶስ 1:21-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከእናንተ ጋር በክርስቶስ ስም የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው። ደግሞም ያተመንና የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ በልቡናችን የሰጠን እርሱ ነው።
2 ቆሮንቶስ 1:21-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ፣ እኛንም እናንተንም በክርስቶስ ጸንተን እንድንቆም የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው፤ የቀባንም እርሱ ነው፤ የርሱ ለመሆናችን ማኅተሙን ያተመብን ደግሞም ወደ ፊት ለምናገኘው ነገር የመንፈሱን ዋስትና በልባችን ያኖረ እርሱ ነው።
2 ቆሮንቶስ 1:21-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥ ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።