መዝ​ሙረ ዳዊት 135:1-21

መዝ​ሙረ ዳዊት 135:1-21 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና። የአ​ማ​ል​ክ​ትን አም​ላክ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና። የጌ​ቶ​ችን ጌታ አመ​ስ​ግኑ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ እርሱ ብቻ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን ያደ​ረገ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ሰማ​ያ​ትን በጥ​በቡ የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ምድ​ርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ብቻ​ውን ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ለፀ​ሐይ ቀንን ያስ​ገ​ዛው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ሌሊ​ትን ያስ​ገ​ዛ​ቸው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ከበ​ኵ​ራ​ቸው ጋር ግብ​ፅን የገ​ደለ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያወጣ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ በጸ​ናች እጅ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ፈጽሞ የከ​ፈለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ እስ​ራ​ኤ​ልን በመ​ካ​ከሉ ያሳ​ለፈ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ፈር​ዖ​ን​ንና ሠራ​ዊ​ቱን በኤ​ር​ትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ሕዝ​ቡን በም​ድረ በዳ የመራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ከዓ​ለት ውኃን ያፈ​ለቀ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ታላ​ላቅ ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ጽኑ​ዓን ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ የአ​ሞ​ራ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥ የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤ ርስት ምድ​ራ​ቸ​ውን ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፥ ለባ​ሪ​ያው ለእ​ስ​ራ​ኤል ርስት አድ​ርጎ የሰጠ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤