“እነሆ፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይሆናልና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፤ ወደ ልብም አይገቡም። ነገር ግን በውስጥዋ ደስታንና ሐሤትን ያገኛሉ፤ እኔም ለኢየሩሳሌም ደስታን ለሕዝቤም ሐሤትን አደርጋለሁ። እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤትን አደርጋለሁ፤ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ በውስጥዋ አይሰማም። ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጐልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ ኀጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና። ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፤ ሌላም እንዲበላው አይተክሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይወት ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላቸዋል። እነርሱ ከእነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም፤ ለርግማንም አይወልዱም።
ትንቢተ ኢሳይያስ 65 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 65:17-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች