መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 5:20-27

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 5:20-27 አማ2000

የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶር​ያ​ዊ​ውን ይህን ንዕ​ማ​ንን ማረው፤ ካመ​ጣ​ለ​ትም ነገር ምንም አል​ተ​ቀ​በ​ለም፤ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በስ​ተ​ኋ​ላው እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች እወ​ስ​ዳ​ለሁ” አለ። ግያ​ዝም ንዕ​ማ​ንን ተከ​ተ​ለው፤ ንዕ​ማ​ንም ዘወር ብሎ ወደ እርሱ ሲሮጥ ባየው ጊዜ ሊገ​ና​ኘው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ፥ “ሁሉ ደኅና ነውን?” አለው። እር​ሱም፥ “ሁሉ ደኅና ነው፦ አሁን ከነ​ቢ​ያት ወገን የሆኑ ሁለት ጐል​ማ​ሶች ከተ​ራ​ራ​ማው ከኤ​ፍ​ሬም ሀገር ወደ እኔ መጥ​ተ​ዋ​ልና፤ አንድ መክ​ሊት ብርና ሁለት መለ​ወጫ ልብስ ትሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ” አለው። ንዕ​ማ​ንም፥ “ሁለት የብር መክ​ሊት ውሰድ” አለው፤ ሁለ​ቱ​ንም መክ​ሊት ብር ተቀ​ብሎ በሁ​ለት ከረ​ጢት ውስጥ ጨመ​ረና ከሁ​ለት መለ​ወጫ ልብስ ጋር ለሁ​ለት ሎሌ​ዎቹ አስ​ያዘ፤ እነ​ር​ሱም ተሸ​ክ​መው በፊቱ ሄዱ። ወደ ስውር ቦታም በደ​ረሱ ጊዜ ከእ​ጃ​ቸው ወስዶ በቤቱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው፤ ሰዎ​ቹ​ንም አሰ​ና​በተ። ከዚ​ህም በኋላ ገብቶ፥ በጌ​ታው ፊት ቆመ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ግያዝ ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣህ?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ወዴ​ትም አል​ሄ​ድ​ሁም” አለ። እር​ሱም፥ “ያ ሰው ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ ሊቀ​በ​ልህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ልቤ ከአ​ንተ ጋር አል​ሄ​ደ​ምን? አሁ​ንም ወር​ቁ​ንና ልብ​ሱን፥ ተቀ​ብ​ለ​ሃል፤ ለወ​ይን ቦታ፥ ለመ​ሰ​ማ​ርያ ቦታና ለዘ​ይት ቦታ፥ ለላ​ሞ​ችና ለበ​ጎች፥ ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ባሮች ይሁ​ንህ። ነገር ግን የን​ዕ​ማን ለምጽ በአ​ን​ተና በዘ​ርህ ላይ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይመ​ለስ” አለው። እንደ በረ​ዶም ለም​ጻም ሆኖ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።