መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 16:1-7

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 16:1-7 አማ2000

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊ​ትም በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ አኖ​ሩ​አት፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረቡ። ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ በፈ​ጸመ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ሕዝ​ቡን ባረከ። ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ለወ​ን​ዱም ለሴ​ቱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አን​ዳ​ንድ እን​ጀራ፥ አን​ዳ​ን​ድም ቍራጭ ሥጋ፥ አን​ዳ​ን​ድም የዘ​ቢብ ጥፍ​ጥፍ አካ​ፈለ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያወ​ድ​ሱት ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ትና ያከ​ብ​ሩ​ትም ዘንድ ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን አቆመ። አለ​ቃ​ውም አሳፍ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ሔል፥ ሰሜ​ራ​ሞት፥ ይሔ​ኤል፥ ማታ​ትያ፥ ኤል​ያብ፥ በና​ያስ፥ አብ​ዲ​ዶም፥ ይዒ​ኤል በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ አሳ​ፍም በጸ​ና​ጽል ይዘ​ምሩ ነበር። ካህ​ና​ቱም በና​ያ​ስና የሕ​ዜ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁል​ጊዜ መለ​ከት ይነፉ ነበር። በዚ​ያም ቀን ዳዊት በአ​ሳ​ፍና በወ​ን​ድ​ሞቹ እጅ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ሰ​ግኑ አስ​ቀ​ድሞ ትእ​ዛ​ዝን ሰጠ።