መጽሐፈ መዝሙር 18:32-35
መጽሐፈ መዝሙር 18:32-35 አማ05
ብርታትን የሚሰጠኝና መንገዴን የሚያቀናልኝ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያጠነክራል፤ በከፍታ ቦታዎችም ያለ ስጋት ለመቆም ያስችለኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ የነሐስን ቀስት መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል። የማዳን ጋሻህን ሰጠኸኝ፤ ቀኝ እጅህም ይጠብቀኛል፤ እኔን ለመርዳት መጥተህ ታላቅ አደረግኸኝ።

