የዮሐንስ ወንጌል 15:15-17

የዮሐንስ ወንጌል 15:15-17 አማ05

አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤ እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል። እንግዲህ እኔ የማዛችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።