ትንቢተ ኢሳይያስ 65:17-23

ትንቢተ ኢሳይያስ 65:17-23 አማ05

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እኔ አዳዲስ ሰማያትንና አዲስ ምድርን እፈጥራለሁ፤ ከዚህ በፊት የነበሩት ሁሉ ይረሳሉ፤ አይታሰቡምም። እኔ ኢየሩሳሌምን ለደስታ ሕዝብዋንም ሐሴተኞች እንዲሆኑ ልፈጥር ስለ ሆነ ለዘለዓለም ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ። እኔም ራሴ በኢየሩሳሌምና በሕዝቤ ደስ ይለኛል፤ ከዚያም በኋላ ለቅሶም ሆነ የዋይታ ድምፅ አይኖርም። በሕፃንነቱ የሚሞት ከቶ አይኖርም፤ ዕድሜውንም የማይፈጽም ሽማግሌ አይኖርም፤ በመቶ ዓመቱ የሚሞት ሰው በወጣትነቱ እንደ ሞተ ወጣት ከመቶ ዓመት በታች የሚሞት ሰው እንደ ተረገመ ይቈጠራል። ሕዝቤ ቤት ሠርተው ይኖሩበታል፤ ወይን ተክለው ፍሬውን ይበላሉ፤ እነርሱ የሠሩትን ቤት ሌሎች አይገቡበትም፤ የተከሉትንም ማንኛውንም ነገር ባዕዳን አይበሉትም፤ ሕዝቤ እንደ ዛፍ ለረጅም ዘመናት ይኖራሉ፤ የመረጥኳቸውም ሰዎች የደከሙበትን ነገር ለረጅም ጊዜ ይደሰቱበታል። ሥራቸው ከንቱ አይሆንም፤ የወለዱአቸው ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በእግዚአብሔር የተባረኩ ስለሚሆኑ ልጆቹን የሚወልዱት ጥፋት እንዲደርስባቸው አይደለም።