ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:5-7

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:5-7 አማ05

እናንተ አገልጋዮች ሆይ! በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑት በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ታዘዙ፤ ለክርስቶስ በምታገለግሉት ዐይነት በልብ ቅንነት ታዘዙአቸው። የምትታዘዙትም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ እንደሚፈጽሙ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች ሆናችሁ ነው እንጂ ሰውን ደስ ለማሰኘት ብላችሁ ለታይታ አይሁን። ሰውን ሳይሆን ጌታን እንደምታገለግሉ አድርጋችሁ በመልካም ፈቃድ አገልግሉ።