ኦሪት ዘዳግም 17:19-20

ኦሪት ዘዳግም 17:19-20 አማ05

ይህን መጽሐፍ አጠገቡ በማኖር በዘመኑ ሁሉ ያንብበው፤ ይህንንም ቢያደርግ እግዚአብሔርን ማክበርና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትንም ሕጎችና ደንቦች በጥንቃቄና በታማኝነት መፈጸምን ይማራል። ራሱንም ከወገኖቹ ከእስራኤላውያን እበልጣለሁ ብሎ እንዳይታበይና ከእግዚአብሔርም ትእዛዞች እንዳይርቅ ይጠብቀዋል። ይህን ቢያደርግ ለብዙ ዘመን ይነግሣል፤ ልጆቹም በእስራኤል ላይ ለብዙ ዘመን ይነግሣሉ።