መዝሙር 105:16-22

መዝሙር 105:16-22 NASV

በምድሪቱ ላይ ራብን ጠራ፤ የምግብንም አቅርቦት ሁሉ አቋረጠ፤ በባርነት የተሸጠውን ሰው፣ ዮሴፍን ከእነርሱ አስቀድሞ ላከ። እግሮቹ በእግር ብረት ተላላጡ፤ በዐንገቱም የብረት ማነቆ ገባ። የተናገረው ቃል እስኪፈጸምለት፣ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው። ንጉሥ ልኮ አስፈታው፤ የሕዝቦችም ገዥ ነጻ አወጣው። የቤቱ ጌታ፣ የንብረቱም ሁሉ አስተዳዳሪ አደረገው፤ ይኸውም ሹማምቱን በራሱ መንገድ ይመራ ዘንድ፣ ሽማግሌዎቹንም ጥበብ ያስተምር ዘንድ ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}