እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ? ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ። ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል። ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤ በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤ መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው። በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል። በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል። አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ። በየመንደሩ ሥርቻ ያደፍጣል፤ ንጹሓንን በሰዋራ ስፍራ ይገድላል። ዐይኖቹንም በምስኪኖች ላይ ያነጣጥራል። በደኑ ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል፤ ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፤ ድኻውንም አፈፍ አድርጎ በወጥመዱ ይጐትታል። ምስኪኑም ይደቅቃል፤ ዐንገቱን ይደፋል፤ ያልታደለውም በክንዱ ሥር ይወድቃል።
መዝሙር 10 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 10
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 10:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች